
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሦስተኛው የሃይማኖት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ኮንፈረንሱ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በጉባኤው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ በሃይማኖት ተቋማት አንድነትን፣ ፍቅር እና ሰላምን ስታስጠብቅ ኖራለች። የሃይማኖት ተቋማት ለጋራ ሀገር የጋራ ታሪክ ሲሠሩ ኖረዋል። ዛሬም እየሠሩ ነው።
የራቀውን እያቀረቡ፣ የተጣላውን እያስታረቁ፣ የላላውን እያጠበቁ የሕዝብ እና የሀገር አንድነት ሲያስጠብቁ ኖረዋል።
ዛሬም የኢትዮጵያን ችግሮችን ለመፍታት፣ ሰላምን ለማምጣት እና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ከእነርሱ በላይ ባለ አደራ እና ባለ ታሪክ የለም። ስለ ሰላም እየመከሩ ሰላምን ያረጋግጣሉና።
የሃይማኖት ተቋማት በአንድነት የተሠባሠቡት ዋናው ዓላማቸው ዘላቂ ሰላምን በሀገር ላይ ለማረጋገጥ ነው።
በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው የሃይማኖት አባቶች ዛሬም በኢትዮጵያ የጸና ሰላምን እንደሚያመጡ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን