
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ለመታደም የአደባባይ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ እየገቡ ነው።
በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። በዛሬው የኮንፈረንስ ውሎው የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊ ይኾናሉ።
ነዋሪዎቹ ከከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ያለልዩነት “ሰላም እንፈልጋለን” የሚሉ ድምጾችን በአደባባይ ሰልፍ እያሰሙ ኮንፈረንሱ ወደሚካሄድበት ስታዲየም እየገቡ ነው።
“ሃይማኖታዊ መሠረቶቻችን የሰላማችን ምንጮች ናቸው፣ የሃይማኖት ተቋማት ሰላምን፣ ፍቅርን እና አብሮነታችንን ያስተሳሰሩ ገመዶች ናቸው፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰላማችንን ለማጽናት የሚያደርገውን ጥረት እንደግፋለን እና መሰል መልዕክቶች በዓደባባይ ሰልፉ ላይ እየተስተጋቡ ነው።
የኮንፈረንሱ ሙሉ ሂደት ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀመር ሲኾን በአሚኮ የማሰራጫ ጣቢያዎች በቀጥታ ወደ አድማጭ፣ ተመልካች እና ተከታዮቻችን ይደርሳል
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን