
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) የመልበስ ግዴታን የሚጥል መመሪያ መጽደቁን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
በብራዚል የነበረው መዘናጋት እና ቸልተኝነት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ ከሌላው ስህተት መማር ብልህነት በመሆኑ ሕጉን ማጥበቅ ማስፈለጉን ገልጸዋል።
‘‘ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለወገን እና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ጥንቃቄያችንን ከበፊቱ በላይ እናጠናክር’’ ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በማኅበራዊ ገጻቸው።
ኅብረተሰቡ ለራሱ ሲል በመንግሥት እና በባለሙያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መመሪያዎች ችላ ሳይል እንዲተገብርና ለሕግ አስከባሪዎች እንዲታዘዝም አሳስበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡
