የሰውነት መነሻ በጎነት በመኾኑ ለስኬታማ ሕይወት በጎነትን ማስቀደም ይገባል።

8

ደሴ: ሰኔ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 13ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ሠልጣኞች ምርቃት መርሐ ግብር “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በደሴ ከተማ ተካሂዷል። ለሦስት ሳምንት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠና ወስደው የተመረቁት አብዱ ይማም እና ሀገሪቱ አያሌው ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የሰውነት መነሻ በጎነት መኾኑን በመረዳት ለስኬታማ ሕይወት በጎነትን ማስቀደም ይገባል ያሉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አወል ሠይድ (ዶ.ር) ናቸው። ዩኒቨርሲቲው የሰላም እና የበጎነት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ ተመራቂዎች ለሰላም ግንባታ ሳይታክቱ መሥራት እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

ማኅበረሰቡም ለሥራቸው አጋዥ መኾን ይገባዋል ነው ያሉት። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አማካሪ ፍሬሰንበት ወልደትንሳኤ በጎነት የዕለት ተዕለት ተግባር መኾን እንደሚገባው ጠቁመዋል። ተመራቂዎች ሀገራዊ መግባባት ላይ አመርቂ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።

በ13ኛው የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ከ5 ሺህ በላይ ሠልጣኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ መሠልጠናቸውም ታውቋል።

ዘጋቢ:- ሕይወት አስማማው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ አብሮነት እና በተባበረ ክንድ ታፍራ እና ተከብራ የምትኖር ታላቅ ስመ ገናና ሀገር ናት” መልአከ ብርሃን ፍስሐ ጥላሁን
Next articleበጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ክትትል እና ቁጥጥር መደረጉ ለውጥ ማምጣቱን የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።