ጉባኤው የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የእርቅ እና የሰላም መልዕክተኞች እንዲኾኑ ያግዛል።

38

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤ ከወራት በፊት በድሬዳዋ አና በጅማ ከተሞች አንደኛውን እና ሁለተኛውን ጉባኤ ማካሄዱን አስታውሰዋል። ዛሬ የጀመረው እና በባሕር ዳር ከተማ የሚካሄደው ደግሞ ሦስተኛው ጉባኤ መኾኑን አንስተዋል።

ጉባኤው አራት ዓላማዎች አሉት ብለዋል ዋና ጸሐፊው። ዓላማዎቹም በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም፣ ችግሮች ሲፈጠሩ በውይይት እና በንግግር መፍታት ለማስቻል፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የእርቅ እና የሰላም መልዕክተኞች እንዲኾኑ ለማገዝ እና ኅብረተሰቡን የበለጠ ለማቀራረብ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብ ማነቃቃት ስለመኾኑ አስረድተዋል።

ይሄ ጉባኤ አንድነታችንን የሚያጠናክር በመኾኑ በሁሉም ክልሎች የሚካሄድ መኾኑን ገልጸዋል።

ጉባኤው በነገው እለትም በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ይቀጥላል። ልዩ ልዩ መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሦስተኛው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
Next article“ስለሰላም መስበክ የሁልጊዜ ተግባር ሊኾን ይገባል” ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ