
ባሕር ዳር: ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል ብለዋል።
በውይይታችን በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አግልግሎት የገቡ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና በሁለተኛው ዙር ለመግባት ዝግጅት ያጠናቀቁ ተቋማትን ቅድመ ዝግጅትን ተመልክተናል፡፡ በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መሶብን ለማስጀመር እያከናወኑ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ ሪፖርትን ገምግመናል ነው ያሉት፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የገቡ ተቋማት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አይተናል ብለዋል፡፡
በቀጣይም በሁለተኛ ዙር ወደ መሶብ የሚገቡ ተቋማት እና በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ ተግባራት እንዴት መሰራት እንዳለባቸዉ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴአቸውም አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን