
ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በሚገኙ በ36 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው።
የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ መቅደስ ብዙነህ በዛሬው ዕለት 2 ሺህ 740 ተማሪዎች በፈተናው ላይ መቀመጣቸውን ነው የገለጹት።
ያነጋገርናቸው የብሩህ ተስፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አብርሃም ተሰማ እና የአቡነ ጎርጎሪዎስ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅድስት ሥላሴ ቅርንጫፍ ርዕሰ መምህር ፍቅሩ የታሸወርቅ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
ፈተናውን በተረጋጋ መንገድ እንዲወስዱና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ደግሞ የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ናቸው።
ፈተናውን በስኬት ለማጠናቀቅም የቅርብ ክትትል እንደሚደረግም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- በላይ ተስፋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!