
ጎንደር: ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር በሰባት የፈተና መስጫ ማዕከላት፣ በ44 ትምህርት ቤቶች ፈተና እየተሰጠ ነው። ከ6 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መኾኑንም የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ስንታየሁ ነጋሽ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ለፈተና ዝግጁ እንዲኾኑ በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲሠራ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ስንታየሁ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ሲደረግ ከነበረው ክትትል እና ድጋፍ በተጨማሪ የሥነ ልቦና ግንባታ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በግል ሲያደርጉት ከነበረው ትጋት ባሻገር መምህራኖቻቸው በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉላቸው መቆየቱን ለአሚኮ የተናገሩት ደግሞ በጻድቁ ዮሐንስ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፈተና ሲወስዱ ያገኘናቸው ተማሪ ሚኪያስ ኢዲሱ እና ተማሪ ሳራ ለምለሜ ናቸው።
ተማሪወቹ በጥረታቸው ልክ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እየጣሩ መኾኑንም ነግረውናል። በፈተና ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የተገኙት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ፈተናው በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከተማ አሥተዳደሩ በትኩረት እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ተማሪዎች በፈተናው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ወላጆች ፣ መምህራን እና የትምህርት ተቋማት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም መልዕክት ተላልፏል።
ዘጋቢ፦ አዲስ ዓለማየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን