የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ምሰሶ ነው።

16

አዲስ አበባ: ሰኔ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የውጭ ጉዳይ እና የኢኮኖሚ ሴክተሮች ቅንጅታዊ ጉዞ ለተቃና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ” በሚል መሪ መልዕክት የከፍተኛ ባለሙያዎች እና መሪዎች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አዲስ አማራጭን ለማሰስ፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ዲፕሎማሲውን ለማጎልበት ያለው ሚና እና የተቋማት ትብብርን ለማጠናከር ዓላማ ያለው ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ድኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ መድረኩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ምሰሶ የኾነውን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አዲስ የመፍትሔ አቅጣጫዎች የሚገኝበት እና ቅንጅታዊ አሠራርን የሚያሳድግ ስለመኾኑ አስረድተዋል።

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ምሰሶ ነው ስንል የሀገራችንን እምቅ አቅም፣ የተፈጥሮ እና የሰው ሃብት ለማጎልበት፣ ለማስተሳሰር እንዲሁም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እንሠራለን ማለት ነው ብለዋል።

የመድረኩ አዘጋጅ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩን ጨምሮ የኢፌዴሪ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ.ር) በመድረኩ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበአማራ ክልል 130 ሺህ 280 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።
Next articleየሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙ በአገልጋይነቱ የላቀ የመንግሥት ሠራተኛ ለመፍጠር አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት የሰሜን ሸዋ ዞን አስታወቀ።