የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ማጣራት ጀመረ።

16

ወልድያ: ሰኔ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ በመንግሥት አሥተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ከከተማና ክፍለ ከተማ የሥራ ኀላፊዎች እንዲኹም ቡድን መሪዎች ጋር ምክክር አካሂዷል።

የመምሪያው ተወካይ ኀላፊ ሲሳይ ብርሃን የከተማ አሥተዳደሩን የሰው ኃይል አቅም በመገምባት የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።

አገልግሎቱን በማዘመን ዲጂታል የማድረግ ሂደት መጀመሩን ነው ያስረዱት። እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን በማጥራት ለክልል ለማድረስ እስከ ቀበሌ ድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማትን ዲጂታል ማድረግ ከተማዋን የማዘመን ዋነኛ ሥራ ነው ብለዋል።

በመኾኑም ከተማ አሥተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በዞን፣ በክልል እና ከተሞች ደረጃ ከተካሄዱ ውይይቶች የቀጠለ ውይይት ዛሬ በፌዴራል ደረጃ አካሂደናል።
Next articleሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለአገልግሎት አሰጣጥ እንቅፋት እየኾነ ነው።