“ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠት የእሳቤ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል” በድሉ ውብሸት

15

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ በመንግሥት አገልግሎት እና ሪፎርም ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ነው። በውይይቱ ላይ የተገኙት የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት “ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠት የእሳቤ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል” ብለዋል።

ለዚህም ይህን መሰል ውይይት እጅግ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተናግረዋል። የመንግሥት ሠራተኛው ባለበት የሙያ መስክ ላይ ውጤታማ ሥራን እንዲያከናውን ሪፎርሙ መሰረታዊ ነጥብ ይዞ መጥቷልም ብለዋል። በከተማዋ ላለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ የመንግሥት ሠራተኞች ያላቸው ትጋት ትልቅ ሚና ስለመጫወቱም ነው የተናገሩት።

ከብልሹ አሠራር የፀዳ ሥርዓትን በማስፈን አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባም አሳስበዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ እስክንድር ገብረሚካኤል ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የመንግሥት ሠራተኞች አሥተዳደር መዘመን አለበት ነው ያሉት።

በቀጣይነትም በተጠያቂነት መርኾች መመራት እንዳለበትም አንስተዋል። ለውጡን ዕውን ለማድረግ ውጤታማና ተወዳዳሪ፤ ሀገራዊ የመንግሥት አገልግሎትና አሥተዳደር መገንባት የሚያስችል ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል። በውይይቱ ከከተማ አሥተዳደሩ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ያሉ የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ:- ወንዲፍራ ዘውዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገር አሸናፊ የምትኾንበት ዘዴ መመካከር ነው።
Next articleባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ቦታዎች ላይ ያለውን የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ በትብብር እየሠሩ ነው።