ማኅበረሰቡ የራሱን ሰላም እንዲጠብቅ የሚያስችል ውይይት በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

7

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ውይይቱ በከተማዋ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ስድስት ቀበሌዎች ነው እየተካሄደ ያለው።

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ማኀበረሰብ ተኮር ውይይቶችን በተደጋጋሚ በማድረግ የከተማዋ ነዋሪዎች የራሳቸውን ሰላም እንዲጠብቁ ለማትጋት እየተሰሠራ ነው ብለዋል።

የዘረፋ፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎች መበራከት የከተማዋን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲያውክ ቆይቷል፤ ነዋሪዎች የሰላሙ ባለቤት እንደኾኑ በመግባባት የከተማዋን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማጽናት መቻሉንም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ አመራሮች እና ነዋሪዎች በተቀናጀ መንገድ በመሥራታቸው ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በክፍለ ከተማው ካሁን በፊት የማጭበርበር እና የማታለል ወንጀልን ጨምሮ እገታ እና የተቀናጀ ዝርፊያ ይፈፀም እንደነበር የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሠራዊት በዛ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ግን ከኅብረተሰቡ ጋር በተደረገ ተደጋጋሚ ውይይት የአካባቢውን ረላም ማጽናት መቻሉን አስረድተዋል።

የወንጀሎቹ መበራከት በከተማዋ የወደፊት የማደግ ተስፋ ላይ መሰናክል እንዳይኾን ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎችም ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- ብርቱካን ማሞ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዓለም አቀፉ የቤተሰብ ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next articleከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በወረታ ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።