
ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ “የተሻሻለ የቤተሰብ ሥራና ገቢ ለሀገር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ መልዕክት ክልላዊ የቤተሰብ ቀን የማጠቃለያ ዝግጅት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ በአማራ ክልል ምክር ቤት የሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበራሽ ታደሰ እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በቤተሰብ ቢዝነስ አጀማመር፣ የቤተሰብ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት፣ በቤተሰብ ግጭት አፈታት፣ የቤተሰብ የሥራ ባሕልና ተነሳሽነትን ማዳበር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዩች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!