
እንጅባራ: ሰኔ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአዊኛ ራዲዮ የጀመረበት 20ኛ ዓመት በዓል በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አማካሪ ግዛቸው ሙሉነህ፣ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ፣ የወረዳዎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር አባላት እንዲሁም ከየወረዳው ማኅበረሰቡን የወከሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን