ከፍተኛ መሪዎች በአዲስ ዘመን ከተማ አሥተዳደር የተገነባውን ትምህርት ቤት መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

22

ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ አሥተዳደር የተገነባውን ትምህርት ቤት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ቤት ምክትል አፈጉባኤ አማረ ሰጤ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የተገነባው ትምሕርት ቤት 28 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ትምህርት ቤቱ ባለ አራት ወለል ሕንጻ ነው። በውስጡ 25 የመማሪያ ክፍሎች አሉት። ትምህርት ቤቱ በኅብተሰቡ ተሳትፎ፣ በዳሽን ቢራ ፋብሪካ እና በአማራ ልማት ማኅበር ትብብር የተገነባ መኾኑ ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ዘመን መክፈቻ ነው!
Next articleየወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያበለፀገውን መተግበሪያ በወልድያ ከተማ ሥራ አስጀመረ።