ምርኩዝ በጎ አድራጎት ማኅበር የዒድ አል አድሃ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ድጋፍ አደረገ።

13

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጎ አድራጎት ማኅበሩ በባሕር ዳር ከተማ በቋሚነት ለሚደግፋቸው እና ለሌሎች በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ 400 የኅብረሰብ ክፍሎች ነው ድጋፍ ያደረገው።

ምርኩዝ በጎ አድራጎት ማኅበር በቋሚነት ለሚደግፋቸው 150 አቅመ ደካሞችና ለሌሎች ለችግር ተጋላጭ 250 የእስልምና እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል።

የምርኩዝ በጎ አድራጎት ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ ሀያት አግራው ማኅበሩ ከተመሰረተ ከአምስት ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ጠቁመው ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሃብት በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረጉ መኾናቸውን ተናግረዋል።

1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

ማኅበሩ እንዲሰፋ እና በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ እንዲያደርግ ሌሎች ድርጅቶችና ተቋማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ሃያት አሳስበዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ሰብዕና ግንባታ ባለሙያ ወርቅነህ እንዳለው ወጣቶች የሃይማኖቱን አስተምህሮ በመከተል ለተቸገሩ ወገኖች እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚበረታታ መኾኑን ገልጸዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ዋና ሰብሳቢ ሙሃመድ ኡስማን ምርኩዝ የበጎ አድራጎት ማኅበር ላደረገው ድጋፍ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ወቅቱ ችግር የበዛበት በመኾኑ ኅብረሰቡ መደጋገፍና መረዳዳት ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

1ሺህ 446 ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በባሕር ዳር ከተማ አብሮነትን እና መተሳሰብን በማጎላት ተከብሯል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየሕዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ግዳጃችንን በብቃት እየተወጣን ነው።
Next article“በአንድነት ስትነሱ ሰላማችሁን አረጋግጣችሁ ታሪክ ትሠራላችሁ” አቶ ይርጋ ሲሳይ