
ወልድያ: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 446ኛው የአረፋ በዓል በወልድያ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጸሐፊ ኡስታዝ ሀሰን ተማም ሕዝበ ሙስሊሙ ከሶላት መልስ የሚኖረውን ዕርድ ሃይማኖቱ በሚፈቅደው ሥርዓት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንዲያካፍል አሳስበዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ሕዝበ ሙስሊሙ በከተማዋ ልማት እና ብልጽግና የድረሻውን እንዲወጣም ነው የጠየቁት።
በተለይም ወቅታዊውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ ከከተማው ነዋሪ ውጭ የመፍትሄ አካል የለም ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሕዝበ ሙስሊሙ ሰላምን ከልብ በመሻት እንደ ከተማ ነዋሪ ለሰላም መጽናት የሚጠበቅበትን እንዲያበረክትም ነው ያሳሰቡት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን