የዘምዘም ውኃ

10

የእናትን ጥረት እና የልጅን ጩኸት ሰምቶ ፈጣሪ በምድረ በዳ መካከል ያፈለቀው የሕይዎት ውኃ ናት

የሚጠጣት ባይኖር ሞልታ አትፈስስም፤ የሚጠጣት ቢበዛ ምንጯ አይደርቅም ከዓለም ዙሪያ ሐጂ የሚያደርግ ሙስሊም ጠጥቷት እና ቀድቶ ወደየሀገሩ ወስዷት ዛሬም ድረስ ከልክ አታልፍም፤ ከወሰኗም አትጎድልም

የአሏህ እዝነት እና የመላዒካ ተራዳዒነት የተስተዋለባት የሕይዎት ውኃ ናት

ማንኛውም ውኃ ጥምን ሊያረካ ይችላል የዘምዘምን ውኃ የተለየች የሚያደርጋት ግን እንደ ምግብም የምታጠግብም ጭምር መኾኗ ነው

ስትሞላ ራሷ የምታቆም ከተመደበው በላይ የማታመነጭ እና በቀን 691 ሚሊዮን ሊትር ትመነጫለች ለፈውስ የሚውል እና ሃይማኖታዊ ቅቡልነት የላቀ ውኃ ከሃይማኖት አልፎ ሳይንስ ሳይቀር ተመራጭነቱን አረጋግጧል ከብክለት የጸዳ፣

ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ እና ከመጠጥ አልፎ ለፈውስ አገልግሎት የሚውል ውኃ ነው

Previous articleእስልምና ሃይማኖት ለሁሉም ሰላም መኾንን በአስተምህሮቱ ይገልጻል።
Next articleተስፋ የተጣለበት ልዩ ትምህርት ቤት!