
ደብረማርቆስ: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።
የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነብዩ ኢብራሒም የፈጣሪያቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም እና ልጃቸውን ኢስማኤልን ለመስዋዕት ለማቅረብ በጎ ፈቃድ ያሳዩበትን ለማስታወስ የሚከበር በዓል ነው።
በዓሉ በደብረ ማርቆስ ከተማ በሃይማኖቱ ተከታዮች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸሪያ ፍርድ ቤት ሠብሣቢ ሼህ ወለላው ሰይድ ሕዝበ ሙስሊሙ የነብዩ ኢብራሒምን ታዛዥነት በመላበስ ያለን በማካፈል እና ሃይማኖታዊ ትዕዛዝን በማክበር በዓሉን ማክበር ይገባል ብለዋል።
የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የሰላም በዓል በመኾኑ ሁሉም ለሰላም እና ለአንድነት እንዲሠራ ሼህ ወለላው ሰይድ ጠይቀዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ የዕምነቱ ተከታዮችም ሃይማኖታዊ ትዕዛዛትን በመፈጸም እና የተቸገሩትን በመጠየቅ በዓሉን እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።
በሀገር ሰላም እንዲመጣም በዱኣ ፈጣሪን በመጠየቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ነው የገለጹት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን