የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የዒድ ሰላት ሥነ ሥርዓት በደሴ ከተማ ሆጤ ስታዲዬም ተከናውኗል።

13

ደሴ: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ እንድሪስ በሽር በመላው ዓለም ለሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በዓሉን ሲያከብር አቅመ ደካሞችን እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች በማሰብ መኾን እንዳለበት አሳስበዋል። በተለይ ከዒድ ሰላት በኋላ የኡዱህያ እርድ የሚፈጽሙ ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ሰላም ለሁሉም ነገር መሠረት ነው ያሉት ሼህ እንድሪስ ለሀገራችን እና ለክልላችን ሰላም ዱኣ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። ሰላምን በማስጠበቅ ረገድም ሙስሊሞች የድርሻችንን መወጣት አለብን ነው ያሉት።

ያነጋገርናቸው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዓሉን ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በመጠያየቅ እንደሚያከብሩም ምዕመናኑ ገልጸዋል።

በሆጤ ስታዲዬም በተከናወነው የዒድ ሰላት ላይ የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሼህ እንድሪስ በሽር፣ የደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጅድ ኢማም ሼህ ያዕቆት አብዱልመጅ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ እና ሌሎች የከተማዋ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና ለሀገር ሰላም በመጸለይ መኾን ይገባዋል።
Next article“በትህትና እና በመታዘዝ የቀረበ መስዋዕት”