ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና ለሀገር ሰላም በመጸለይ መኾን ይገባዋል።

16

ከሚሴ: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በከሚሴ ከተማ እየተከበረ ነው።

በበዓሉ የተሳተፉ የከተማው ነዋሪ አማኞች በዓሉን በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደሚያከብሩ ተናግረዋል።

የሃይማኖት አባቱ ኡስታዝ ጦይብ ጀማል ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የሃይማኖቱ አስተምህሮት በሚያዘው መልኩ በመተዛዘን ሊኾን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የእርድ ሥነ-ሥርዓት የሚያካሂዱ የሃይማኖቱ ተከታዮች ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ለሚስኪኖች እና ለተቸገሩ ሰዎች የሚሰጠውን በተገቢው ኹኔታ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸውም ነው ያስገነዘቡት።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም የከተማው ማኅበረሰብ የመደጋገፍ እሴቱን በማጠናከር በአብሮነት በዓሉን እንዲያከብርም አሳስበዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ በበኩላቸው የተገኘው አንፃራዊ ሰላም እንዲፀና ሕዝበ ሙስሊሙ የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ክልሉ ያለውን አቅም አሟጥጠን ስንጠቀም ዕድገት እና ብልጽግናን እናረጋግጣለን” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የዒድ ሰላት ሥነ ሥርዓት በደሴ ከተማ ሆጤ ስታዲዬም ተከናውኗል።