
ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ጀውሐር ሙሐመድ ሕዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን ማጠናከር እንደሚገባው ተናግረዋል።
በጎ ነገር ማድረግ የበዓሉ ቅድመ ሁኔታ መኾኑን ያነሱት ሼህ ጀውሐር ሙሐመድ ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን፣ አቅመ ደካሞችን እና የተፈናቀሉትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመንከባከብ እንዲኾንም ነው ያስገነዘቡት።
እርድ ከሚፈጸመው አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንደሚለገስ ሃይማኖታዊ ግዴታ መኾኑንም ገልጸዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ላበረከተው የመስገጃ ቦታ አመሥግነው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ሁሉም ሕዝበ ሙስሊሙ እንዲተባበር አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሰራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን