
ደብረ ብርሃን: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሃይማኖቱ ተከታዮችም ይህንን ታላቅ በዓል በኅብረት እና ምስኪኖችን በመዘየር እያከበሩ ስለመኾናቸው ተናግረዋል፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ይህንን ታላቅ በዓል ስናከብር በፍፁም መዋደድ እና መረዳዳት መኾን ይገባዋል ብለዋል፡፡
የእርድ በዓል እንደመኾኑ መጠን ለበዓሉ የሚታረደውን ለአቅመ ደካሞች በማካፈል በፍቅር ማሳለፍ ይገባልም ብለዋል፡፡
የሃይማይኖቱ ተከታዮች ከሶላት እና ስግደት በኋላ የዚያራ መርሐ ግብር የሚያከናውኑ ሲኾን በበዓሉ አስተምህሮ መሰረት በዓሉን እያከበሩ ስለመኾናቸው ነው የተናገሩት፡፡
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን