1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ እየተከበረ ነው።

12

ደብረ ብርሃን: ግንቦት 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአረፋ በዓል የመስዋዕትነት በዓል ነው። ነብዩ ኢብራሂም በአሏህ ትዕዛዝ መሠረት ልጃቸው እስማኤልን ለመሰዋዕት ፈቃድ የሰጡበት በመኾኑ።

በዓሉ የመታዘዝ፣ በእምነት የመጽናት እና የመረዳዳት በዓል ተደርጎ ይወሰዳል። አረፋ የእርድ በዓል ነው። ከዒድ ሰላት በኋላ የሃይማኖቱ ተከታዮች እርድ ይፈጽማሉ። ያረዱትን ሦስት ቦታ ይከፍላሉ።

አንድ እጁን ለተቸገረ፣ አንድ እጁን ለዘመድ፣ አንድ እጁን ደግሞ ለቤተሰብ በማድረግ በዓሉን በደስታ ያከብራሉ።

ከዚያ ባለፈ የዚያራ መርሐ ግብር አለ። የሃይማኖቱ ተከታዮች ብቻም ሳይኾኑ የከተማው ነዋሪዎች በጋራ የመተባበር ልምድ እንዳላቸው ነው የነገሩን።

በአሁኑ ሰዓት የሃይማኖቱ አባቶች እና የሃይማኖት ተከታዮች ከከተማ አስተዳደሩ በተረከቡት በአዲሱ የመስገጃ ቦታ የዒድ ሰላት እያደረጉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፦ ደጅኔ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሐጅ እና ኡምራ ጉዞ የሚደረግባት ከተማ- መካ
Next articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በደሴ ከተማ እየተከበረ ነው።