ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

17

ርእሰ መሥተዳድሩ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 446 ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ ብለዋል።

የአረፋ በዓል የእስልምና ዕምነት ተከታዩ በመልካምነት፣ በአብሮነት እና በመተጋገዝ በደስታ የሚያሳልፈው በዓል በመሆኑ በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ታላቅ በዓል መኾኑን ገልጸዋል።

የአረፋ በዓል ሲከበር የአረፋ በዓል ልዩ መገለጫና ቱሩፋቶች የሆኑትን የተራበን የማብላት፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታረዘን በማልበስ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

በዓሉ የሀገራችንን ክብር እና የኅዝባችንን አንድነት የበለጠ የምናጠናክርበት፤ መተሳሰባችንና አብሮነታችንን ከፍ የምናደርግበት እንዲሆንን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት።

Previous articleየሀጂ ሥርዓት ዓለም ስለእኩልነት ልትማርበት የሚያገባ ጠቃሚ እና ገንቢ እሴቶች ያሉት ነው።
Next articleየዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን በባሕር ዳር ከተማ ለማክበር አማኞች ወደ ጋጃ መስክ የዒድ ማክበሪያ ቦታ እየተጓዙ ነው።