
ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮሙኒኬሽን፣ ከሕዝብ ግንኙነት አመራሮች እና የሚዲያ አካላት ጋር የሚደረግ ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ በባሕር ዳር ተጀምሯል።
በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው ( ዶ.ር) እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየን ጨምሮ ሌሎች የክልል መሪዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት፣ ማኅበራዊ እና የተግባቦት ሥራዎች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎች ላይ በመወያየት ግንዛቤ እንደሚያዝባቸው እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ግልጽነት እንደሚፈጠር ይጠበቃል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ በመረዳት ለብሔራዊ መግባባት፣ ለሰላም እና ለልማት እንዲኹም ለሀገር ገጽታ ግንባታ በመትጋት መተባበር እና መሥራት ባለበት ጉዳይ ላይም ውይይት በማድረግ መግባባት እንደሚፈጠር ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን