“ባሕር ዳር በሥራ ላይ ነች” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

30

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት “ባሕር ዳር በሥራ ላይ ነች” ብለዋል።

ዛሬ በከተማዋ ተገኝተን እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕር ዳርን ወደ ምቹ ከተማነት ለማሸጋገር የሚረዱ የመንገድ ግንባታ፣ የኮሪደር ልማት እና የተቋማት ዕድሳት ሥራዎች በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወኑ መኾኑን ተመልክተናል ነው ያሉት።

ከተማይቱን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለቱሪስቶች ተወዳጅ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ከተማዋ ለሚመጡ እንግዶች ደግሞ ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ይበሉ የሚያሰኙ ናቸው፡፡

እነዚህ የተጀመሩ መልካም ተግባራትን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በተጨማሪም ፕሮጀክቶችን በጥራት ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

መንግስት የከተሞች ውበት እና የተጥሮ ሀብት ተጠብቆ እንዲዘምኑና የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር ክትትል እና ድግፍ ለሚሹ ጉዳዮች አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ሕዝብ ትልቁ ጠላት ድህነት እና ኋላቀርነት ነው” ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር)
Next articleየሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ማገዝ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው።