ከተሞችን ለኑሮ ብቻ ሳይኾን ለምርት እና ምርታማነት ምቹ ለማድረግ መሥራት ይጠበቃል።

6

ደሴ: ግንቦት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና የሥራ ፕሮጀክት የልምድ ልውውጥ እና ዐውደ ጥናት በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ በሀገሪቱ ከ88 በላይ ከተሞች የከተማ እና መሠረተ ልማት የሥራ ኀላፊዎች፣ የከተሞች ሴፍቲኔት ባለሙያዎች እና ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት በዓለም ባንክ እና በመንግሥት ትብብር ተግባራዊ እየተደረገ ያለ መርሐ ግብር ነው።

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ መርሐ ግብሩ በከተሞች ዝቅተኛ የገቢ አቅም ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በከተማ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል።

ከተሞችን በመሠረተ ልማት ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባሻገር ለምርት እና ምርታማነት ምቹ እንዲኾኑ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ሚኒስትሯ አሳስበዋል።

በፕሮግራሙ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቀሚ መኾናቸው ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ባለ ዓለምየ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleትምህርት ላይ የገጠመውን ሥብራት ማስተካከል እንደሚገባ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አሳሰቡ።
Next article”ምን ችግር እንደገጠመን ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን ጊዜ ላይ ነን” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)