
ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ”ትውልድ በመምህር ይቀረጻል፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ መልዕክት ክልላዊ የመምህራን ውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተጀምሯል።
በውይይቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና የአማራ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዝዳንት ታጀበ አቻምየለህን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ መሪዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ሀገራዊ እና ክልላዊ የሰላም እና ልማት ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል።
በትምህርት ተደራሽነት እና ጥራት፣ በመጭው ክልላዊ እና ሀገራዊ መልቀቂያ ፈተናዎች አፈጻጸም ላይም ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን