
ጎንደር: ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ የሚካሄደውን “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄን ክልላዊ የመዝጊያ ዝግጅት ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
መሪዎቹ ጎንደር ከተማ ሲደርሱ የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል።
መሪዎቹ ዛሬ ግንቦት 26/2017 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የሚካሄደውን የ2017 ዓ.ም ክልል አቀፍ “የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። በመድረኩ መክፈቻ ላይም በቲቲኬ ኢንዱስትሪያል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባውን ቲቲኬ ዘይት ፋብሪካ መርቀዋል።
ፋብሪካው ከዘይት በተጨማሪ ለኬክ መጋገሪያ ግብዓቶችን እና የተለያዩ የሳሙና ዓይነቶችን ያመርታል።
ቲቲኬ ዘይት ፋብሪካ አኩሪ አተር እና ሌሎችንም የግብርና ምርቶች በስፋት በመጠቀም ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ፋብሪካ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን