
ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አራተኛውን እና የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ አካል የሆነውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ አስጀምረናል። እነዚህ መኖሪያዎች ተገንብተው ሲጠናቀቁ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘዬ የሚቀይሩ እና ጤናማ ሕይወትን የሚያላብሱት ናቸው።
በሌላ በኩል በዞኑ በነበረን ቆይታ የግሉ ዘርፍ በአግሮ ኢንደስትሪ ላይ ያለውን ተሳትፎ ተመልክተናል። እንደማሳያ አቶት የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪን ተዘዋውረን ተመልክተናል። እንዲህ ያሉት ስራዎች በሌማት ትሩፋት ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ተግባር ከግብ ለማድረስ በጎ ጅምሮች በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን