
ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት በከተማ የተጀመሩ የክረምት በጎ ፍቃድ ልማት ሥራዎች ከገጠሩ ክፍል ጋር የማስተሳሰር አካል በኾነው የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራ እያስጀመርን ነው ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ዱባንቾ ቀበሌ በገጠር ኮሪደር ሞዴል የአርሶ አደሮች መኖሪያ መንደር የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
እነዚህ ማሳያ መንደሮች መገንባታቸው አርሶ አደሩ የግብርና ሥራ እያከናወነ የተሻለ ሕይዎት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!