ከ27 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን እንደሚወስዱ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

12

እንጅባራ: ግንቦት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መምሪያው በመጪው ሰኔ ወር በሚሰጠው ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ዙሪያ ለባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ ፈጥሯል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው ዓለሙ 27 ሺህ 605 ተማሪዎች ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ድጋፎች እየተደረገላቸው እንደኾነም ገልጸዋል።

መምህራን ትርፍ ጊዜያቸውን ሁሉ ተጠቅመው ተማሪዎችን ለማብቃት ከሚያደርጉት ድጋፍ ባሻገር በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ማረፊያ ክፍሎችን በማዘጋጀት ውለው አድረው እንዲያጠኑ እየተደረገ ነውም ብለዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ እና ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ አይተነው ታዴ ጤናማ ያልኾነ የምዘና ሥርዓት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እንቅፋት መኾኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎች፣ የወላጆች እና አጠቃላይ የትምህርት መዋቅሩ የረጅም ጊዜ ልፋት ሰላማዊ እና ደኅንነቱ ተጠብቆ እንዲጠናቀቅ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃልም ነው ያሉት።

ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ የሥነ ልቦና ግንባታ እና የድጋፍ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ግፋ በለው እያሉ ከማዋጋት ይልቅ ተው እያሉ መመለስ ለሕዝብ ይበጃል”
Next article“እናንተ ሰላምን ካስከበራችሁ የልማት ሥራዎች ይቀጥላሉ” ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ