እስከ 12 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቃይ ቤተሰቦች ዛሬ ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው።

325

በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ከ11 ሺህ እስከ 12 ሺህ ቤተሰቦች ዛሬ ወደ መተከል ዞን ዳንጉርና ማንቡክ ወረዳዎች እየተመለሱ ነው።

ባለፈው ዓመት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተቀስቅሶ በነበረ ግጭት ከ49 ሺህ በላይ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ነበር። ከእነዚህ ውስጥ እስከ 12 ሺህ ቤተሰቦች (በግለሰብ ደረጃ ከ30 ሺህ በላይ) ዛሬ ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የሁለቱ ክልሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ነው ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ቀየ መመለስ የጀመሩት።

ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከተመለሱ በኋላ መንግሥት ከሚያደረግላቸው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ ለቀጣይ ዓመት በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ ዘር እንዲቀርብላቸውም ጠይቀዋል።

የቀጣናውን ሰላም ወደ ነበረበት ለማምጣት በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ከተቋቋመ ወዲህ አንጻራዊ ሠላም ተፈጥሯል።

ከዚህ በፊት ከ9 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለሳቸው ይታወሳል። በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት እስከዚህ ወር መጨረሻ ሁሉንም ተፈናቃዮች ለማቋቋም አቅዶ እየሠራ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡

Previous articleየበርሃ አንበጣ መስፋፋቱ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ሳይገታ ከቀጠለ እስከ 30 ሚሊዮን ሕዝብ ለተረጅነት እንደሚጋለጥ አቶ አብርሃም አለኸኝ ገለጹ፡፡
Next articleበአማራ ክልል 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ ከእነዚህ መካከል 7 ሰዎች አገግመዋል፡፡