የገጠሩን ማኅበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው የገጠር ኮሪደር በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።

8

ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንቢጣ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የኾኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን አስጀምረዋል።

ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ እና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርሶ አደሩም ጤናማና ክብር ያለው ሕይዎት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

በአካባቢው ከ2 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ቀደም በጎርፍና ድርቅ አደጋ ይታወቅ የነበረውን አካባቢ የልማት ተምሳሌት ያደርገዋልም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፍተኛ ልዑክ ከሱዳኑ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተገናኙ።
Next articleበፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ሊሰጥ ነው።