
ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብሔራዊ መረጃ እና ደህንት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተላከ መልዕክትን ለሱዳኑ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሀን አቀረቡ።
መልዕክቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ በፖርት ሱዳን ተገኝተው አቅርበዋል።
በፖርት ሱዳን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የገለፁት የልዑኩ መሪ “ሱዳን ሰላም እና መረጋጋቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ኢትዮጵያ የማይናወጥ ድጋፏን እንደምትቀጥል” በአጽንኦት መግለጻቸውን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!