
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፌዴራል ተቋማት እና ማኅበራት ደረጃ የተካሄደው 14ኛው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ስኬታማ መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።
የሂደቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በ11 ክልሎች እና በሁለት የከተማ አሥተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ማካሄዱን ተናግረዋል።
14ኛውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በፌዴራል ተቋማት እና በማኅበራት ደረጃ መካሄዱን ጠቁመው ይህም ስኬታማ መኾኑን ገልጸዋል።
በፌደራል ተቋማት እና ማኅበራት የተካሄደው የምክክር ምዕራፍ ከ38 በላይ ተቋማት መሳተፋቸውንም ተናግረዋል።
እስካሁን የተሰበሰቡ ሁሉም አጀንዳዎች ወደ ኮሚሽኑ ቋት መግባታቸውን ተናግረዋል። በአጀንዳዎቹ ላይ በዋናው የምክክር ጉባኤ ጊዜ መግባባት ላይ እንደሚደረስባቸውም ገልጸዋል።
በቀጣይ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት የሚከናወን መኾኑን ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በምክክር ሂደቱ ላይ የማሳተፍ ሥራም ቀሪ የኮሚሽኑ ሂደት መኾኑን መናገራቸውን ከኢዜአ ዘግቧል።
በሌላ መልኩም እስካሁን በሂደቱ ላይ ያልተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ሌሎች አካላትን ወደ ሂደቱ እንዲመጡ ይሠራልም ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን