
ባሕርዳር፡ ግንቦት 17/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በተደረገ 2 ሺህ 844 የላቦራቶሪ ምርመራ 73 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 655 ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ የተገኘባቸው በ49 ወንዶች እና በ24 ሴቶች ነው፤ እድሜያቸው ደግሞ ከ6 እስከ 75 ዓመት መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዜግነታቸውም 67 ኢትዮጵያዊ፣ ቀሪዎቹ የስድስት ሀገራት ዜጎች መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ገልጧል፡፡
መኖሪያቸው ደግሞ 56 ከአዲስ አበባ (13 ሰዎች በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ያላቸው፣ 12 የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 31 ሰዎች የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በበሽታው ከተያዙ ጋር ንክኪ ስለመኖራቸውም ያልተረጋገጡ)፣ አራት ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው)፣ ሁለት ሰዎች ከአማራ ክልል (በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው)፣ ስምንት ሰዎች ከሶማሌ ክልል (የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ ሦስት ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ሰባት ሰዎች አገግመዋል፡፡ ያገገሙትም አራት ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ ሁለት ከትግራይ ክልል እና አንድ ከአዲስ አበባ ናቸው ብሏል ጤና ሚኒስቴር፡፡
በዚህም አጠቃላይ ያገገሙት 159 ደርሰዋል፤ በቫይረሱ የተያዙት ደግሞ 655 ናቸው፡፡