የደሴ ሙዚየም እድሳትና ጥገና ተደርጎለት ዳግም አገልግሎት መሰጠት ጀመረ።

13

ደሴ: ግንቦት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ሙዚየም በ1909 በደጃዝማች ዮሴፍ ብሩ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የተገነባ ሲኾን ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ በሙዚየምነት እያገለገለ ይገኛል።
ሙዚየሙ የወሎ አካባቢ ማኅበረሰብን እሴት፣ ባሕል እና ቅርስ ይዞ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ሙዚየሙ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት እና ዘረፋ ተፈጽሞበት አገልግሎት መስጠት አቁም ቆይቷል። ሙዚየሙ ዳግም አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ከብሪቲሽ ካውንስል እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ባገኙት ድጋፍ ጥገና እና እድሳት ተደርጎለት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

ሙዚየሙን መርቀው የከፈቱት በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)፤ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ስለሽ ግርማ፣ የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋዬ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር እና የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በጋራ በመኾን ነው።
በደሴ ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ድረስ የሉሲ እና የሰላም ቅሪተ አካልን ጨምሮ በሙዚየሙ የሚገኙ ቅርሶች ለነዋሪዎች የሚታይበት መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።
ዘጋቢ:- ሰይድ አብዱ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ በእውቀት እና በስነ ልቦና ዝግጁ መኾናቸውን ተማሪዎች ተናገሩ።
Next articleከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደብረ ታቦር ከተማ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።