
ወልድያ: ግንቦት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በደቡብ ወሎ ዞን ከደላንታ ወረዳ እና ወገልጤና ከተማ አሥተዳደር ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወገልጤና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እያካሄዱ ነው።
በውይይቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሐ ደሳለኝ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሻምበል ፈረደ ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን