የከተማዋን ሰላም ዘላቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

10

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከቀበሌ ጀምሮ ከሚገኙ መሪዎች ጋር የተልዕኮ አፈጻጻም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አስቻለ አላምሬ፣ የአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት እሱባለው መሰለ፣ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን እና ሌሎች መሪዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት የራስን ሰላም በራስ አቅም መጠበቅ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። የከተማዋን የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት። ውይይቱ እስከ ጎጥ ድረስ በመውረድ አስተማማኝ ሰላምን ለማጽናት የሚያስችል መኾኑን ተናግረዋል።

ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎን የሕዝብ ግንኑነት መሠራቱንም ተናግረዋል። ከሕዝብ ጋር እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች ያመጡትን ለውጥ በጥልቀት መገምገም እንደሚገባም ገልጸዋል።

ውይይቶች ለሰላም እና ለልማት ሥራ የፈጠሩትን አወንታዊ ለውጥ መገምገም እንደሚገባም ከንቲባው አመላክተዋል።

በውይይቱ የከተማዋ አገልግሎት አሰጣጥ እንደሚገመገም ገልጸዋል። የመሪዎች ቁርጠኝነት እና የአመራር ብቃትም በውይይቱ እንደሚገመገም ነው የተናገሩት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next articleሥጋ ደዌ በሽታ በባክቴሪያ እንጅ በዘርም አይተላለፍም፤ እርግማንም አይደለም።