
ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የኢዩቤልዩ ቤተ መንግሥትን ከጎበኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተነጋግረናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽዖ እንድታበረክት መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣ ገልጬላቸዋለሁ ነው ያሉት።
አዲስ ለተመደቡት ብጹአን አባቶች መልካም የሥራ ዘመንም ተመኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን