ከአድማጮች ጋር የነበረውን መስተጋብር በማጠናከር አሁንም ማኅበረሰቡን ማገልገሉን ይቀጥላል።

14

ደብረ ብርሃን: ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተለያዩ ሚዲዬሞችን በማቋቋም የክልሉን ሕዝብ የሚዲያ ፍላጎት ለማርካት እየሠራ ይገኛል፡፡ ከ11 ዓመታት በፊት ያቋቋማቸው የደሴ እና የደብረ ብርሃን ኤፍ ኤም ጣቢያዎች በየዕለቱ በሬዲዮ ሞገድ ለአድማጭ ተደራሽ እየኾኑ ዛሬ ላይ ደርሰዋል። ጣቢያዎቹ የተመሠረቱበትን 11ኛ ዓመት እያከበሩ ነው።

አማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ሬዲዮ ጣቢያ በየዕለቱ የስድስት ሰዓት የቀጥታ ስርጭት የሬዲዮ ሽፋን እየሰጠ ነው፡፡ የአማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ሬዲዮ ጣቢያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮሐንስ ንጉሥ ጣቢያው ከጊዜ ወደ ጊዜ የተደራሽነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከሬዲዮ ስርጭት በተጨማሪ በቴሌቪዥን ሽፋን የደብረ ብርሃን ከተማ እና ሰሜን ሸዋ ዞንን ተደራሽ በማድረግ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ፤ የልማት ተግባራት እንዲስፋፉ የበኩሉን እየተወጣ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ አዳዲስ የፕሮግራሞች እና የዜና ለውጥ በማድረግ የአድማጭ እና ተመልካቾችን ፍላጎት ለማርካት እየተሠራ እንደኾነም አስረድተዋል፡፡

አሚኮ ቀጣይነት ያለው ለውጥ በማምጣት መንግሥት እና ሕዝብ የበለጠ መቀራረብ የሚችሉበትን አውድ ለመፍጠር እየተሠራ እንደኾነም ገልጸዋል። ያለፉትን 11 ዓመታት ከአድማጮች ጋር የነበረውን መስተጋብር በማጠናከር አሁንም ማኅበረሰቡን ማገልገሉን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የአካባቢውን የሚዲያ ፍላጎት በማርካት በኩል የተጫወተው ሚና ቀላል አይደለም ብለዋል።

በቀጣይ ጊዜያትም የአድማጭ ተመልካቹን ሃሳብ በማዳመጥ በተሻለ አገልግሎት ለመምጣት የለውጥ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት። የአማራ ኤፍ ኤም ደብረ ብርሃን 91.4 ሬዲዮ ጣቢያ በአሚኮ ሁሉም ሚዲዬሞች የዘገባ ሽፋን እየሰጠ ሲኾን የትብብር ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ጨምሮ ሌሎች የሚዲያ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleስለሰላም የሚመክር ሀገር አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው።
Next articleበምዕራብ ጎጃም ዞን የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክቶች፦