የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የምርጫ ምዝገባ ማስጀመሪያ (ሹራ)እያካሄደ ነው።

42

አዲስ አበባ: ግንቦት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መርሐ ግብሩ “ምርጫ ለጽኑ ተቋም” በሚል መሪ መልዕክት እየተካሄደ ነው። ከ7 ሺህ በላይ የፌደራል እና የክልል መጅሊስ ዑለማዎች፣ የምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈፃሚ አባላት እና ዐሊሞች ተገኝተዋል። ቦርዱ በአራት ዘርፍ ለተከፋፈሉት የሰሜን፣ የደቡብ፣ የምስራቅ እና የማዕከላዊ ዘርፍ ምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ ሰነድ ርክክብ አካሂዷል። አስመራጮችም እውነተኛ አካታች እና ፍትሐዊ ምርጫን ለማካሄድ ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱላዚዝ ኢብራሂም ፈቶ (ዶ.ር) የሙስሊሙን ጠንካራ ተቋም የመገንባት ጥያቄ ለመመለስ ምርጫውን ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ በማካሄድ ይህንን ታሪካዊ እድል መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ላለፉት 50 ዓመታት ሲንከባለል የቆየውን ጥያቄ መቋጫ ለማበጀት ቦርዱ ያለፈውን ሦስት ዓመታት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት የሚያስችሉ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንም ሰብሳቢው ጠቅሰዋል። የምርጫ አስፈፃሚዎችም በስኬት በማጠናቀቅ ለሀገር ልማት እና እድገት መረጋገጥ የገቡትን ቃል ጠብቀው የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ተቋሙ ከወራት በኋላ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ የአዳዲስ አመራሮች ምርጫ በመላ ሀገሪቱ እንደሚካሄድም ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየቃብትያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ወደ ሥራ የማስገባት ሂደቱ ውጤታማ ነው ተባለ።
Next articleየፋይናንስ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን በማስፈን ልማትን በአሳታፊነት እና ዘላቂነት ማረጋገጥ ይቻላል።