
ወልድያ: ግንቦት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ክፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የሽምሽሀ 023 ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ኘሮጀክት እና በግብርና ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ወጣቶች እንቅስቃሴን ነው የጎበኙት።
የላስታ ወረዳ አሥተዳዳሪ ለዓለም ብርሃኑ የንፁህ መጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ግምባታው ከከርሰ ምድር የሚመነጭ እና 200 ሺህ ሊትር የሚይዝ የውኃ ጋን መኾኑን አስረድተዋል። ይህም በ64 ሚሊዮን ብር በጀት እየተሠራ ስለመኾኑ ነው ያስገነዘቡት።
የበጀት ምንጩ ጂሲኤፍ ኘሮጀክት ሲኾን የክልሉ ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ለወረዳው በሰጠው ኀላፊነት ግምባታው እየተሠራ መኾኑን አሥተዳዳሪው ገልጸዋል። ሥራው 75 በመቶ የተጠናቀቀ ሲኾን 7ሺህ 500 ሕዝብ ተጠቃሚም ያደርጋል ነው ያሉት።
ከወጭ ቆጣቢ እና ከአረንጓዴ ልማት አኳያ ታሳቢ ተደርጎ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ነውም ብለዋል።ግምባታው በ30 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንደሚጀምርም ተመላክቷል። የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶቸ አኳያ በበጀት ዓመቱ በአራት ኢንተርኘራይዝ የተደራጁ 35 ወጣቶች እየሠሩት ያለን የግብርና ሥራም መሪዎቹ ጎብኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን