
ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ከአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና ጄሥራ ኢትዮጵያ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር “መከባባርን እና አብሮነትን በማጎልበት ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል ርእሰ ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ ምክክር እየተካሄደ ነው።
በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ ሐጂ መስዑድ አደም ሃይማኖቶች ለመከባበር እና ለአብሮነት ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነው ብለዋል። የሃይማኖት ተቋማት ዋነኛ ዓላማም ሰላምን በመገንባት የሰላምን ድልድይ ማጠናከር እንደኾነም አስገንዝበዋል።
የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አለኸኝ መለሰ የታመመውን የአማራ ክልል ሰላም ለመፈወስ የሃይማኖት አባቶች ሌሊት እና ቀን የሚሠሩ ሐኪሞች መኾን አለባቸው ነው ያሉት።
የሃይማኖት አባቶች የማይግባቡ አካላትን የማግባባት ታሪካዊ ኀላፊነትም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን