የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች ውጤታማ ሥራዎች ተሠርተዋል።

27

ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ማሥተባበሪያ ዕቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው። በክልሉ የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸው በመድረኩ ተገልጿል።

የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራምን ተደራሽነት ለማስፋት አበረታች ሥራዎች የተሠሩ መኾኑም ነው በቀረበው ሪፖርት የተብራራው። በፕሮግራሙ የተገኙ ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎችም ወረዳዎች በማስፋት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ባለድርሻ እና አጋር አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸውም ተመላክቷል።

በግምገማ መድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም የርእሰ መሥተዳድሩ አማካሪ ባዘዘው ጫኔ እንዲኹም የፌዴራል የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ማሥተባበሪያ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ወኪሎች እና ሌሎች የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleባሕላዊ የሽምግልና ሥርዓቶችን በመደገፍ ለበርካታ ችግሮች መውጫ መንገድ አድርጎ መጠቀም ይገባል።
Next articleሕጻናት መብታቸው እስከ ምን ድረስ ነው?