ምሁራን ለሀገራዊ እና አካባቢያዊ ችግሮች የመፍትሄ አካል መኾን አለባቸው።

13

ደብረ ማርቆስ: ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ትውልድ በመምህር ይቀረጻል፤ ሀገርም በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ መልዕክት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መሪዎች እና መምህራን ውይይት አድርገዋል።

የትምህርት ተቋማት ብቁ፣ ተወዳዳሪ እና ገበያው የሚፈልገውን በመልካም ሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ መፍጠር ተቀዳሚ ዓላማቸው ነው። በዕለቱ ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር የተቋማት የአቅም ግንባታን በተመለከተ ውይይት ተደርጎበታል።

“ምሁራን የማኅበረሰቡን ችግሮች በጥናት እና ምርምር በመለየት ሀገራዊ መፍትሔ አመላካች ሊኾኑ እንደሚገባ” በውይይቱ ተነስቷል። የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እና የኑሮ ውድነትን መቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚገባም ተነስቷል። መምህራን ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የእርስ በርስ ግጭቶች እንዲቆሙ መውጫ መንገድ አመላካች ሊኾኑ እንደሚገባም ተጠይቋል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳይሕ ካሰው (ዶ.ር) የሠለጠነ የሰው ኃይል በመቅረጽ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራን በማጠንከር ማኅበረሰቡ ካለበት ማኅበራዊም ኾነ የሥነ ልቦናዊ ቀውስ እንዲወጣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ኅላፊነት መኾኑን ገልጸዋል።

የደብረ ማረቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አሁን የገጠመንን ቀውስ በሚገባ በመረዳት ከእርስ በእርስ ግጭት ለመውጣት የመፍትሄው አካል ልትኾኑ ይገባል ብለዋል።

የዜጎች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው የተረጋጋ እና ሰላማዊ ሁኔታ ሲፈጠር በመኾኑ መብት እና ግዴታን የተረዳ ማኅበረሰብ በመፍጠር ከግጭት አዙሪት የምንወጣበትን መንገድ ማመላከት ከምሁራን ይጠበቃል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleማኅበረሰቡ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ በመሥራት ከወባ በሽታ ራሱን እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
Next articleባሕላዊ የሽምግልና ሥርዓቶችን በመደገፍ ለበርካታ ችግሮች መውጫ መንገድ አድርጎ መጠቀም ይገባል።