ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ከዊ ቢውልድ ግሩፕ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር ተወያዩ።

33

ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በጣልያን የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከዊ ቢውልድ ግሩፕ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከዊ ቢውልድ ግሩፕ (Webuild Group) ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተገናኝተን እየተሳተፉባቸው ባሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

በጥቂት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቀዉ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በኮይሻ ግድብ ፈጣን አፈጻጻም እንደታየው ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት ረገድ ከWebuild Group ጋር ያለን ትብብር ወሳኝ ነው።

በዛሬው ውይይታችን በመሠራት ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አፈጻጻም ፣ በፍጥነት በታገዘ ውጤታማነት ላይ ፈጠራን እና ዘላቂነትን የሥራዎቻችን ማዕከል አድርገን መያዝ እንደሚገባ ተነጋግረናል ነው ያሉት። ውይይታችን የኢኮኖሚ እድገትን በመምራት እና የረጅም ጊዜ ልማትን በመደገፍ ሀገር የሚያሻግሩ ፕሮጀክቶችን በመከወን ረገድ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባረቀ ነበር ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየግል እና የአካባቢ ንጽሕናን በመጠበቅ ኮሌራን መከላከል እንደሚገባ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
Next articleማኅበረሰቡ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ በመሥራት ከወባ በሽታ ራሱን እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።