ለኮሪደር ልማት የሚያስከፍለው ክፍያ አለመኖሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን አስታወቀ።

9

ባሕር ዳር: ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ለኮሪደር ልማት የሚሠበሠብ ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የደንበኞች አገልግሎት ተሳትፎ እና ቅሬታ አያያዝ ቢሮ ሥራ አሥኪያጅ አምሳሉ ሲሳይ አገልግሎት አሰጣጣቸውን አስመልክተው መግለጫውን ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ተቋማቸው ለተገልጋዮች በግልጽ ካሳወቀው ክፍያ ሌላ የሚሠበሥበው ክፍያ አለመኖሩን ገልጿል።

ደንበኞች በተቋሙ የክፍያ ታሪፍ መሠረት እንዲከፍሉ የሚደረጉት የፍጆታ ሂሳብ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኤጀንሲ የአሥተዳደር ክፍያ፣ ከኢቢሲ ጋር በገባው ውል መሠረት የሚከፈል እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ክፍያ መኾናቸውን አብራርተዋል።

ከኅብረተሰቡ ለተነሱት የታሪፍ ጨመረብን ጥያቄዎች አቶ አምሳሉ ሲመልሱም ኅብረተሰቡ በተለያየ ምክንያት ክፍያዎችን አለማወቅ ካልኾነ በስተቀር አዲስ የተጨመረ ክፍያ አለመኖሩን ነው የገለጹት።

ለኮሪደር ልማት ከከተማ አሥተዳደሩ ጋር በመቀናጀት የሚሠበሠብ ምንም አይነት የኮሪደር ልማት ክፍያ እንደሌለም ነው ሥራ አሥኪያጁ የገለጹት።

ተቋሙ በየጊዜው የሚያወጣቸውን አሠራሮች ለደንበኞቹ በተለያዩ አማራጮች እንደሚያሳውቅ የገለጹት ሥራ አሥኪያጁ ደንበኞች ቅሬታ ሲኖራቸው እና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካባቢያቸው ባሉ ማዕከላት እና በሌሎች አማራጮች ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየኪንታሮት ሕመም ይድናል?
Next article“ኢንቨስተሮች ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ጊዜው አሁን ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ